About This Book
የሰማይ ድንበር፣ የበረሃው እቶን እና የነፍስ ጥሪ
ታሪክ የሚጀምረው ሰው በተወለደበት ቀን አይደለም፤ ታሪክ የሚጀምረው ሰው ለራሱና ለሰብአዊነቱ የሚከፍለውን ዋጋ መረዳት በጀመረበት ቅጽበት ነው! ከሺህ ዓመታት በፊት፣ ታላቋ ንግሥት ማክዳ በነሐስና በጥቁር እንጨት በተጌጠው ወርቃማ ሰረገላዋ ላይ ሆና ከመናገሻዋ እስከ ሰሜኑ ድንበር ድረስ የግዛቷን ወሰኖች ስታስምር፣ ለዚህች ምድር ዘጠኝ ቅዱሳን ስሞችን ሰጥታ ነበር፦ ኤትራያ፣ ዴሳራ፣ ካምቤልያ፣ ባታሪያ፣ ደብራን፣ አዲራ፣ ሜራሳ፣ ቶሳራ እና ጢታራ!
ንግሥቲቱ በብራና ላይ አስጽፋ በድንጋይ ላይ ያስቀረጸቻቸው እነዚህ ስሞች ተራ የቦታ መጠሪያዎች አልነበሩም፤ የትውልዶች እጣ ፈንታ፣ የመከራና የድል፣ የፍቅርና የመስዋዕትነት ምስጢራዊ ኮዶች እንጂ!
ዓመታት አልፉ፤ ዘመናት ተቀየሩ... ነገር ግን የነዚያ ቦታዎች መንፈስና ጥሪ አልጠፋም።
የሁለት ነፍሳት ቅዱስ ቃል ኪዳን
በዘመናችን፣ በዚሁ በጥንታዊው የኤትራያ ምድርና እሳት በሚተፋው የባታሪያ በረሃ መካከል፣ አንድ የሕክምና ሳይንስ ሊቅ ዶክተር አቡበከር ነጭ ካባውንና ያደገበትን ሀገር ተሸክሞ በሞትና በሕይወት መካከል ባለች ቀጭን ክር ላይ ለመራመድ ተገደደ።
በዚያ አስከፊ የስደት መንገድ፣ በየመን አሸዋማ መቃብሮች እና በጥይት እሩምታ መካከል፣ በዓለም ላይ ካሉ ታላላቅ ፍቅሮች ሁሉ የበረታ አንድ ቅዱስ ትስስር ተወለደ። ሶፊያ! ፊቷ በጥቁር ኒቃብ የተሸፈነ፣ ዓይኖቿ ግን የመከራንና የፍቅርን ጥልቅ ባህር የሚያዩ ውብ ነፍስ።
አቡበከር ለሶፊያ ሕይወቱን አሳልፎ ሰጠ፤ ሶፊያ ደግሞ ለአቡበከር የሕይወትንና የሙያውን ጥልቅ ትርጉም አስተማረችው፦ “እጆችህ አሉ። እውቀትህም አለ... ሰውን አትርሳ!” ሞት ሶፊያን ከአቡበከር እቅፍ ውስጥ ነጥቆ ሲወስዳት፣ ታሪኩ ሁለት እስኪመስለው። ነገር ግን የሶፊያ ሞት ማብቂያ አልነበረም—የታላቅ ተጋድሎና የነፍስ ትንሣኤ መጀመሪያ እንጂ!
የሕሊና መስታወት እና የዓለም መድረክ
በስደት፣ በስቃይ፣ በሆስፒታል ኮሪደሮች እና ከሞት በኋላ በሚከተለው ጥልቅ የሕሊና ቅዠት (Bereavement Hallucination) መካከል አልፎ፣ አቡበከር የሶፊያን ምስል በልቡ፣ የዶክተር ናታንን ጥበብ በአእምሮው፣ እና የዶክተር ሰናይትን አጋርነት በጎኑ አድርጎ እስከ ጄኔቫ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አዳራሾች ድረስ ተጓዘ። በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ሲቆም፣ አቡበከር ተራ ሐኪም አልነበረም። እርሱ የሺህዎች ስደተኞች ድምፅ፣ የተሰበሩ እናቶች እንባ፣ እና የተረሱ ሕፃናት ተስፋ ነበር! የንግሥት ማክዳ የሰረገላ አዋጅ፣ በባታሪያ በረሃ የተቀበረው የሶፊያ ፍቅር፣ በደብራን ብርድ መካከል የሚበራው የከዋክብት ብርሃን፣ እና በሜጀራ እናት እጅ ላይ የወደቀው የ300,000 ብር ተስፋ ሁሉም ወደ አንድ ታላቅ እውነት ይመራሉ፦ “ሕክምና ሳይንስ ነው። ጤና ሥርዓት ፖሊሲ ነው። ሆስፒታል ተቋም ነው። መድኃኒት መሣሪያ ነው። ከእነዚህ ሁሉ በላይ ግን... ሕክምና ሰው ነው!”
ለአንባቢ የቀረበ የነፍስ ጥሪ
ይህን መጽሐፍ ገልጣችሁ ማንበብ ስትጀምሩ፣ ተራ ታዛቢ ሆናችሁ አትቀጥሉም።የንግሥት ማክዳ የሰረገላ መንቀጥቀጥ ይሰማችኋል፤ የካምቤልያና የባታሪያ እሳት የሚተፋው የበረሃ አሸዋ እግራችሁን ያቃጥለዋል፤ በሞትና በሕይወት መካከል የተቀሰፈችው የሶፊያ ደካማ ትንፋሽ በጆሯችሁ ላይ ያቃጭላል፤ የዶክተር ናታን ጥበብ የተሞላበት ድምፅ ደግሞ የሕሊናችሁን በር ድብደብ አድርጎ ይሞግተዋል። ይህ ታሪክ ሰውን ከሰውነቱ፣ ሐኪሙን ከታካሚው፣ ሥርዓቱን ደግሞ ከዜጋው ጋር የሚያስታርቅ ታላቅ የሕይወት መስታወት ነው። ገጻቱን ገልጡ፤ ወደዚሁ ድቅስ የሚያደርግ፣ ነፍስን የሚያንጻ እና ከአንካራ እስከ ጄኔቫ፣ ከባታሪያ እስከ ደብራን የሚዘልቀው ታላቅ የጥበብና የሕይወት ጉዞ አሁኑኑ ግቡ!
Release Date31 October 2026
LanguageAmharic